You can read this post in English

በግንቦት 28፣ 2023 በተካሄደው የዘንድሮው የSEED ድርጅት ዝግጅት ላይ የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም ርዕሰ ጉዳይ በተለይም በወጣቶች መካከል በድብቅ የተሰራ ሰው ሰራሽ ኦፒዮይድ አጠቃቀም ዋና መድረኩን ወስዷል። በዝግጅቱ ላይ የህክምና ባለሙያ እና የክብር እንግዳ የሆኑት ዶ/ር ሊሻን ካሳ የኦፒዮይድ ችግር በዲኤምቪ (ዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮ አካባቢ ኤምዲ/ቪኤ) በወጣቶች ላይ እንዴት ተጽእኖ እያሳደረ እንደሆነ ስጋታቸውን ለማካፈል መድረኩን ተጠቅመዋል። የባህሪ ጤና ነርስ እና የወጣቶች ተሟጋች የሆኑትን ወ/ት ሉላዴይ ክንፈ ሚካኤልን ወደ መድረክ ተጋብዞዉነበር።

ወይዘሪት ሉላዴይ በዚያ ወር መጀመሪያ ላይ በመድኃኒት ከመጠን በላይ በመጠቀሙ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በበዓሉ ላይ ንግግር ለማድረግ ታስቦ የነበረውን ውዷ ጓደኛዋን ሮቤል ሀብተማርያምን (ሮቤል ሙዚቃ) ወክለው ንግግር አድርገው ነበር። ወይዘሪት ሉላዴይ በአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም ምክንያት ሞተው ስለተገኙ ሰዎች ልባዊ መልእክት አስተላልፈዋል። በቅርቡ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመረቀ አልጋው ላይ ሞቶ ስለተገኘ የአንድ ወጣት ልጅ ታሪክ ተናገረች። ብዙዎቹ የወጣቱ ቤተሰብ አባላት ምርቃቱን ለማክበር ከሀገር ውጭ እና ከኢትዮጵያ ተጉዘው የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን የቀብር ስነ ስርዓቱን እያዘጋጁ ይገኛሉ። በመቀጠልም በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች በሰው ምን ይለኛል አስተሳሰብ የተጠመዱ እና የልጆቻቸውን ፈተናዎች ችላ በማለት ወደ ማገገሚያ ስለመሄድ ለወላጆቻቸው ተናግረው በሰው ምን ይለኛል ጆሮ ዳባ ልበስ ስለተባሉ ልጆች አስረድታለች።

ሰው ሰራሽ ኦፒዮይድ – ፌንታኒል አጠቃቀም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ሁሉም የሀገር ውስጥ  የአካባቢ ጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ኤጀንሲዎች መረጃ በተለይም በወጣቶች ዘንድ የአጠቃቀም ጭማሪን ያረጋግጣል። ይህ የአጠቃቀም መጨመር ከመጠን በላይ የመጠቀም ችግር ላለባቸው ሰዎች ሞት አስተዋጽኦ አድርጓል። እያንዳንዱ ትውልድ የራሱ መጥፎ ባህሪ አለው, ነገር ግን ይህ ትውልድ ሁለተኛ እድል በማይሰጥ ሰው ሰራሽ ናርኮቲክ ተይዟል:: ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ለመነጋገር የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እና ናሎክሶን ኪት በቤታቸው እንዲኖራቸው ያስፈልጋል: በአደጋ ጊዜ ድንገተኛ ሁኔታ ሲከሰት ከመጠን በላይ መጠቀምን ለማርከስ ከፌንታኒል አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የደረት መገተር ሲንድሮም (WCS) ለመከላከል ይረዳል። ሌላ ከዚህ ጋር ተያይዞ ማሪዋና አጫሾች ፌንታኒል ተቀላቅሎ የሚገኝባቸው መሆኑ ነው። እባክዎን ለበለጠ ቪዲዮ ይመልከቱ። 

ስለ ጤና እና ደህንነት ተጨማሪ ጽሁፎችን ለማግኘት በፌስቡክ @TheMosebTimes ላይ ይከተሉን እና ላይክ ያድርጉን።

Related

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.
Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.
error: